TEKHAF Trading PLC
supply Chain Management Team Leader
About this role
የስትራቴጂ እና የፕላን ዝግጅት የድርጅቱን ዋና አላማ ያማከለ የሳፕላይ ቸይን ስትራቴጂ፣ ፖሊሲ እና መመሪያዎችን ማዘጋጀትና መተግበር። የፍላጎትና የአቅርቦት ትንበያ (Demand and Supply Forecasting) በመስራት የቁሳቁስ እጥረት ወይም ትርፍ እንዳይከሰት ማቀድ። የዕቃዎች/ምርቶች ግዥ፣ ማከማቸት እና ስርጭት ዕቅዶችን ማዘጋጀት። 2. የዕለታዊ ሥራዎች እና ኦፕሬሽን አስተዳደር የዕቃ ዝርዝር እና መጋዘን ቁጥጥር (Inventory Control): በመጋዘን ውስጥ ያሉ ዕቃዎች መጠን፣ ጥራት እና ደህንነት መከታተል፤ የዕቃ ብክነትን፣ መበላሸትን እና ስርቆትን መቀነስ። የግዢ እና አቅርቦት ክትትል: አስፈላጊ ቁሳቁሶች እና ጥሬ ዕቃዎች በሰዓቱ መግዛታቸውን እና መድረሳቸውን ማረጋገጥ። የሥርጭት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር (Logistics & Distribution): ዕቃዎች ከፋብሪካ ወይም ከመጋዘን ወጥተው ለደንበኞች ወይም ለቅርንጫፎች የሚሰራጩበትን መንገድ እና የትራንስፖርት ሁኔታ ማመቻቸት። የአቅራቢዎች (Vendors) ግንኙነት: ከአቅራቢዎች ጋር ጥሩ የሥራ ግንኙነት መፍጠር፣ ትዕዛዞች በሰዓቱ መድረሳቸውን መከታተል እና የተፈጠሩ ችግሮችን መፍታት። 3. የሥራ ሂደት ማሻሻል እና ደህንነት (Process Improvement & Safety) ወጪን መቀነስ እና ቅልጥፍናን መጨመር: በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚታዩ አላስፈላጊ ወጪዎችን እና የጊዜ ብክነቶችን ለይቶ ማረም (Lean / 5S አሰራሮችን በመጠቀም)። የሕግ እና ደህንነት መስፈርቶችን ማክበር: በመጋዘን እና በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት የሥራ ቦታ ደህንነት እና የጤና ህጎች መጠበቃቸውን ማረጋገጥ። ሪፖርት ማቅረብ: የዕቃ እንቅስቃሴን፣ የሎጂስቲክስ ወጪዎችን እና አጠቃላይ የአቅርቦት ሰንሰለት ሁኔታን የሚያሳዩ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ለከፍተኛ አመራር ማቅረብ። 4. የግዥ እና የአቅራቢዎች አስተዳደር (Procurement & Supplier Management) ጥራት ያላቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በወቅቱ የሚሰጡ አቅራቢዎችን (Suppliers/Vendors) መለየት እና መምረጥ። ከአቅራቢዎች ጋር የዋጋና የውል ድርድር ማድረግ (Contract Negotiation)። የአቅራቢዎችን የስራ አፈፃፀም እና የውል ግዴታ ማከበር በየጊዜው መገምገም (Supplier Performance Evaluation)። 5. የመጋዘንና የኢንቬንቶሪ አስተዳደር (Inventory & Warehouse Management) በድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ያሉ ዕቃዎች በተገቢው ሁኔታ መያዛቸውን እና ቁጥጥር መደረጉን ማረጋገጥ። የስቶክ እጥረት (Stockout) ወይም ከመጠን በላይ ዕቃ ማከማቸት (Overstocking) እንዳይኖር የኢንቬንቶሪ ደረጃዎችን ማመጣጠን። በየጊዜው የዕቃ ቆጠራ (Stock Counting) ማካሄድ እና ከሲስተም መረጃ ጋር ማነፃፀር። 6.የሎጂስቲክስ እና የስርጭት አስተዳደር (Logistics & Distribution) ዕቃዎች ከአቅራቢ ወደ ድርጅት፣ እንዲሁም ከድርጅት ወደ ደንበኞች የሚጓጓዙበትን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መስመር ማመቻቸት። የጉምሩክ ስነ-ስርዓቶችን፣ ከውጭ ሀገር የሚገቡና የሚወጡ (Import/Export) ዕቃዎችን ሂደት መከታተልና ማፋጠን። የትራንስፖርት እና የስርጭት ወጪዎችን መቆጣጠር እና ማነስ። 7.የቡድን መሪነት እና የሰው ሀይል ልማት እና አስተዳደር (Team Leadership) ቡድኑን መምራት እና ማስተባበር: በሥሩ ያሉትን የመጋዘን ሰራተኞች፣ የሎጂስቲክስ አስተባባሪዎችን እና የግዢ ባለሙያዎችን ዕለታዊ ተግባር ማቀድ እና መከታተል። ስልጠና እና አቅም ግንባታ: ለአዲሶች እና ለነባር ሰራተኞች ለቡድኑ አባላት የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን መስጠት እና ማመቻቸት። የሥራ አፈጻጸም ምዘና (Performance Evaluation): የቡድን አባላትን የሥራ አፈጻጸም መገምገም፣ ግብ ማስቀመጥ እና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ። 8.የስጋትና የወጪ አስተዳደር (Risk & Cost Management) በሳፕላይ ቸይን ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን (ምሳሌ፡ የእቃ መዘግየት፣ የዋጋ ጭማሪ፣ የመንገድ ችግሮች) አስቀድሞ መለየት እና የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ። አጠቃላይ የሳፕላይ ቸይን ወጪዎችን መተንተን እና ወጪ ቆጣቢ አሰራሮችን መዘርጋት። የሀገሪቱን የንግድና የሎጂስቲክስ ህጎች እንዲሁም የድርጅቱን መመሪያዎች ማከበር እና ማስከበር።
Application details and requirements are maintained by the original employer or listing site.